የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-03/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ሎት |
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች |
ኮተቤ ጋራዥ |
በቁጥር |
4 |
የመነሻ ዋጋውን 20% |
ጥቅምት 11 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 |
ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EEU Minor Account No, 1000068699332) የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የንብ ባንክ ዋናው መ/ቤት 10ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመደበኛ የስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ኮተቤ ጋራዥ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ሜከሲኮ አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የንብ ባንክ ዋናው መ/ቤት 10ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-1-26-52-55/011-1-70-01-18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
