Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ ከፍለ ከተማ የሙዳ ፉሪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ዙር ለ2018 ዓ.ም የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን ፤ የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር የሙዳ ፉሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት




 

                                                                                    የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ ከፍለ ከተማ የሙዳ ፉሪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ዙር ለ2018 ዓ.ም የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን ፤ የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡  

የተወዳዳሪዎች መስፈርት 

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  2.  ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ 

  3. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ 

  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነው መቀበል አለባቸው፡፡ 

  5. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ መሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት መቅረብ አለባቸው፡፡ 

  6. የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ₁5 የስራ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከሙዳ ፉሪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሴቶች ማዕከል ህንጻ ውስጥ መግዛት ይቻላል፡፡ 

  7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሙዳ ፉሪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛኑ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ 

  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩበትን የእቃ ብዛት ተባዝቶ 2% በባንክ በተመሰከረ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው ፡፡ 

  9. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ 

  10.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  11. ተጫራቾች በፈለጉትና ማቅረብ በሚችሉት ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ አሸናፊ ተጫራች/ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት እስከ 7ኛ ቀን ቀርቦ ውል ካልፈረመ ማስከበሪያ ያስያዘው ይወረስበታል፡፡ 

  12. ያስቀመጥነው ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል፡፡ 

  13. ተጫራቾች በጨረታ ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎችን ሙዳ ፉሪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ፡፡ 

  14. ተጫራቾች ጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታውን መከፈት አያግድም፡፡ 

  15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ የምትገኘው ጀሞ 2 የሴቶች ማዕከል ህንጻ ውስጥ 

ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር /0912058863/0912081543/0920350135/0912873283 

                                                  በፉሪ ክ/ከተማ አስተዳደር የሙዳ ፉሪ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender