Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የፈሳሽ ናይትሮጂን ማሽን መለዋወጫ ዕቃ፣ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ዶሮ መና መመገቢያና ውሃ መጠጫ፣ ለእንስሳት ጤና ክሊኒክ ለላብራቶሪ ሥራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁስ፣ ንብ ለሚያነቡ የሚያስፈልግ ቁሳቁስ፣ የዓሣ መኖ እና የሐር ልማት ቁሳቁስ ሕጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (Sidama National Regional Government Livestock Development Office)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 02/2018

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የፈሳሽ ናይትሮጂን ማሽን መለዋወጫ ዕቃ፣ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ዶሮ መና መመገቢያና ውሃ መጠጫ፣ ለእንስሳት ጤና ክሊኒክ ለላብራቶሪ ሥራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁስ፣ ንብ ለሚያነቡ የሚያስፈልግ ቁሳቁስ፣ የዓሣ መኖ እና የሐር ልማት ቁሳቁስ ሕጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉና የምዝገባ ምስከር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ከጎርጋዳ ሰፈር ከፊ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ/እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸው አማካይነት መግዛት ይቻላል፡፡
  3. በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /Bank Guarantee/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  4. አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴከኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ኬዝ ቲም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
  10. የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  11. በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-16-10-83-60/ 09-16-07-00-57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

አድራሻ፡- ጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን፡፡

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ

 

Save Tender