የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ሰሚት ጤና ጣቢያ የተለያዩ ጥገና ስራዎች ሊያሰራ ላቀደው ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ሰሚት ጤና ጣቢያ የተለያዩ ጥገና ስራዎች ሊያሰራ ላቀደው ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ከላይ በተጠቀሰው በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ
- ሎት 1 የተለያዩ ጥገና ስራዎች
- የወረዳ 05 ሰሚት ጤና ጣቢያ የግንባታ ስራ ተቋራጭ ደረጃ GC-6, BC-6 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ረዳት ፋይናንስ ክፍል ድረስ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የሥራ 10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፤ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ አርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሽያል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴከኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ _ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ 4ተኛ ፎቅ ግዢ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን በ11ኛዉቀን (አስራ አንደኛዉ) ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ /technical proposal / እና ፋይናንሻል ሰነድ /financial proposal /ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት/technical proposal / በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) ሎት 1.
7. 40000 (አርባ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላለት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝርዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል ፡፡
9. ከትንሹ ግምት በታች እና የተጋነነ ዋጋ ያስገባ ተቋራጭ ብሬከዳውን (BREAKDOWN) ማስገባት እንደሚገደድ እናሳውቃለን፡፡
10. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ ግዢ ቡድን በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል ፡፡
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ስድራሻ ፡- ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሰሚት ጤና ጣቢያ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ሰሚት ጤና ጣቢያ
