Tender Detail

Tender Details


በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጂንካ/ አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤት የቢሮ አላቂ ዕቃዎች እና ጽ/መሣሪያ፣ የፈርኒቸር፣ የኤሌክትሮኒከስ፣ የእንስሳት መድሐኒት እና የህከምና ቁሳቁስ እና ሞተር ሣይከል ግዥ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጂንካ/ አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤት የቢሮ አላቂ ዕቃዎች እና ጽ/መሣሪያ፣ የፈርኒቸር፣ የኤሌክትሮኒከስ፣ የእንስሳት መድሐኒት እና የህከምና ቁሳቁስ እና ሞተር ሣይከል ግዥ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው:- በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ፤ የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ እና ለእንስሳት መድሐኒት እና የህከምና ቁሳቀስ ግዥ ሌሎች ፍቃዶች እንዳሉ ሆነው በዘርፉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የጂ/ከ/አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ ምስከር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶከመንቶች ኦርጅናሉን ከኦርጅናሉ ጋር ኮፒውን ከኮፒው ጋር በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን/ የቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽ/መሣሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ የኤሌክትሮኒክስ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የፈርኒቸር 10,000፣ የእንስሳት መድሐኒት እና የህከምና ቁሳቁስ 6,000 /ስድስት ሺህ ብር /እና የሞተር ሣይክል 10,000 /አስርሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ኦርጅናል ዶክመንታቸውን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ስራ ለመፈፀም ያሸነፈበት ገንዘብ 10 % ሲያሲይዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ወይም ቀኑ በስራ ቀን ካልዋለ በማግስቱ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አይስተጓጎልም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር 0467750256 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በኣሪ ዞን የጂ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender