በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የተዘረዘሩት ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የተዘረዘሩት ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ሎት1. ደንብ ልብስ- ------------ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት2. የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ እቃዎች ---------- 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት3. ህትመት ------------ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት4. መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት --------------- 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት5. የጽዳት እቃዎች --------------- 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት6. የህክምና መገልገያ ማሽኖች ------------- 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
- ሎት7. እንጨትና የብረት ውጤቶች ------------ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት8. ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ------------- 30,000 (ሰለሳ ሺህ ብር)
ከተለያዩ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። በዚህ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው
የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከጤና ጣቢያው በገዙት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ሁሉንም መረጃዎች በሚገባ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም። አስቸጋሪ ሁኔታ ከገጠመ የቀድሞው ቁጥር ሊነበብ በሚችልበት ሁኔታ በአንድ መስመር ብቻ ይሰርዙት።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአቅርቦት ዘርፍ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ እንዲሁም የግርጌ ድምር በመደመር የጠቅላላውን ዋጋ ማሳየት አለባቸው። የሚሞሉት የነጠላና ጠቅላለ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን /VAT/ ጨምሮ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ቃሚ ዕቃ ከሆነ ለሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ የአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናሉንና የሌሎች ማስረጃዎችን ለብቻው በአንድ ፖስታ፤ ሲፒኦ ደረሰኝ በአንድ ፖስታ፣ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ኮፒ በአንድ ፖስታ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በጀርባቸው ላይ ኦሪጅናል፣ ኮፒ፣ እንዲሁም ሲፒኦ በሚል መጻፍና እንደገና ሁሉንም ለብቻቸው የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በፖስታው ጀርባ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒ ሲ.ፒ.ኦ በሚል መግለጽ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ በሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያዳንዱ ገጽ ላይ እና በየደረጃው በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን የበላይ ኃላፊ ፊርማና ሥም እንዲሁም ህጋዊ ክብ ማህተም ማሳረፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘረ መሰረት የሞሉትንና ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀውና በጤና ጣቢያው የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 414 በተቀመጠው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- በተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት የማጭበርበር (የሙስና) ተግበር ሲፈጽሙ ቢገኙ ወይም ለመፈጸም ቢሞክሩ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገው ተፈጸሚ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሂደት ለማዛባት ቢሞክሩ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው ይሰረዛሉ ፤ በቀጣይም በመንግስት ግዥዎች እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን እቃ የሚመለስ ናሙና ከጨረታው መክፍቻ ቀን በፊት ለጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ክፍል በአደራ ማስረከብ አለባቸው። ናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩ እቃዎችን ፎቶ ግራፊና ዝርዝር መግለጫቸውን በማያያዝ ማቅረብ ይችላሉ።
- ማሳሰቢያ፡- ናሙና ሲያመጡ (ሲያቀርቡ) የድርጅቱ ማህተም መደረግ የለበትም፤ ነገር ግን ምልክት አድርጎ ያቀረበ አቅራቢ የመጣው ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ተጫራች ውል እስኪገባ ድረስ ተመላሽ አይሆንም።
- የጨረታ ሳጥንኑ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰው ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩት በመጀመሪያ በዕቃ ጥራት ሲሆን በሁለተኛው ደረጃ የሚያቀርቡት ዝቅተኛ የዋጋ መጠን ሆኖ ሁለት ተጫራቾች አኩል ነጥብ ቢያመጡ የግዥ መመሪያና ደንቡ ተፈጻሚ ይሆናል።
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራች ያሸንፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ /CPO / ሲፒኦ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ውል ሲፈጽምም ሆነ ከተፈጸመ በኋላ በጨረታው ሰነዱ ላይ ከሞሉት ዋጋ ውጭ ምንም አይነት ማስተካኪያ ማድረግ አይቻልም ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ የሚፈጹምላቸው እንዲያቀርቡ የታዘዙትን ዕቃ በታዘዙበት ጊዜ በራሳቸው ወጪ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ሲያስረክቡና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሲያቀርቡ ነው።
- በግዥ አፈጻጸሙ ላይ በደል ደርሶብኛል የሚል ተጫራች ለአቤቱታው መሰረት የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5/አምስት / የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ጨረታ ላወጣው የመንግስት መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል። የበላይ ኃላፊው መልስ ካልሰጠ ወይም በሚሰጠው መልስ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ ውሳኔው መስጠት ከነበረበት ጊዜ ገደብ ማብቂያ ጀምሮ በሚቆጠር 5/አምስት / የስራ ቀን ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ለአጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል። ከዚህ ጊዜ በኋላ ለአጣሪ ኮሚቴው የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም።
- መሥሪያ ቤቱ ከተጫራቹ ጋር ከገባው የግዥ ውል አቅርቦት መጠን ላይ በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀር እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል ።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-68-61-09-20 ወይም ቢሮ ቁጥር 414 በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
- አሸናፊ ወይም አቅራቢ ድርጅት የአሸነፈበትን እቃ ገቢ ለማድረግ ደረሰኝ ሲያቀርብ የካሽ ሪጅስተር ከአታችመንት ጋር (የእጅ በእጅ ደረሰኝ) ከሆነ ከገቢዎች ደረሰኝ እንዲጠቀሙ የተፈቀደበት ደብዳቤ ማጻፍ አለባቸው ይህ ካልሆነ ግን እቃውን ገቢ ማድረግ የማይቻል መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን።
- ከጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ አቅራቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈው መምጣት ያለባቸው ከአደራጃቸው የጽ/ቤት የበላይ ሃላፊ ተፈርሞ መቅረብ አለባቸው። ነገርግን በቡድን መሪ ተፈርሞ የሚመጣ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም።
ማሳሰቢያ
- ጥቃቅን አነስተኛ ለተደራጁ አቅራቢዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት (ዕቃ) ብቻ መሆኑን አውቀው የአምራች (አቅራቢ) የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
- ነገር ግን በማያመርቱት ምርት (ዕቃ) መወዳደር የሚችሉት እንደማንኛውም ተጫራች ሲፒዮ ማቅርብ (ማስያዝ) አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ግዜ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመንግስት በስራ ሰዓት ጤና ጣቢያ አራተኛ ፎቅ ረዳት ፋይናንስ ክፍል ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
ጥብቅ ማሳሰቢያ
- መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት የሚወዳደሩ አቅራቢዎች፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፍኬት ማቅረብ አለባቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት
- የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ cpo (ሲፒዮ) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለምሳሌ ቢድ ቦንድና የባንክ ጋራኒቲ ቢቀርብ በምንም ተቀባይነት እንደማይኖረው በትህትና እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
