በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ የተለያዩ ኤሌክተሮኒክስ ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን
የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ የተለያዩ ኤሌክተሮኒክስ ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሚፈለጉት ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን አይነትና ብዛት
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ተንቀሳቃሽ ስልክ (Galaxy Samsung A16, 128 GB, 8 RAM 8, 5th Generation |
ቁጥር |
8 |
|
2 |
ኮምፒዩተር (HP laptop Computer Core i5, 15.6 inch, 8 GB RAM, SSD 512, 12th Generation |
ቁጥር |
6 |
|
3 |
ኮምፒዩተር (HP laptop Computer Core i7, 14 inch, 1TB SSD, 16 GB RAM, 13th Generation |
ቁጥር |
1 |
|
4 |
ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተር (Dell Desktop computer Core i3) |
ቁጥር |
1 |
|
5 |
ፕሪንተር (Hp printer With scanner, HP Leaser MFP 135W) |
ቁጥር |
2 |
ስለሆነም የተዘረዘሩትን የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን አይነትና ብዛት ማቅረብ የምትችሉ እንዲሁም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ከዚህ በፊት የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አቅርቦት ላይ ስርተው የሚያውቁ ለዚህም ካቀረቡላቸው ድርጅቶች የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ወይም ቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ከላይ በተራቁ ከ1-3 የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ህጋዊ በሆነ የድርጅታቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በማስፈር በድርጅታቸው ማህተምና ፊርማ አረጋግጠው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አዲስ አባባ በሚገኘው የኮሚሽናችን መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአስረኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ኮሚሽኑ በተጫራቾች የቀረበውን ጨረታ ሰነድ ላይ የሰፈሩትን የቴክኒክና የፋይናንስ ዝርዝሮችን ከገመገመ በኋላ የጨረታው አሸናፊ የሆነውን ድርጅት ያሳውቃል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከኮሚሽነ· ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ በተነገረው በ5 ቀናት ውስጥ የኤልክትሮኒስ ቁሳቁሶችን ትክክለኛነት እና በአግባቡ መሰራታቸውን በኮሚሽናችን ባለሞያዎች ፍተሻ ካስደረገ በኋላ ቁሳቁሶችን የኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ቁሳቁሶቹን አቅርቦ ለኮሚሽኑ እንዳስረከበ በ5 ቀናት ውስጥ ክፍያ ይፈጸምለታል።
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፡ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት
በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ
ኮሚሽን ጽ/ቤት
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ 0910006953/0912122895
አዲስ አበባ
