Tender Detail

Tender Details


በማእከላዊ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግሥት በሥልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ከታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግሥት በሥልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግሥት በሥልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ከታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. ሎት 1፦ የተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል፣

2. ሎት 2፡- የደንብ ልብስ፥

3. ሎት 3፦ እስቴሽነሪ እና የቢሮ አላቂ እቃዎችን፣

4. ሎት 4- የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ኤል ሲዲ እና ሌሎችን)፡

5. ሎት 5፡- የተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል ስፔር ፓርት፣

6. ሎት 6፡- የፈርኒቸር እቃዎችን፣

7. ሎት 7- ጀነሬተር፣

በዚህም መሰረት ማንኛውም ሕጋዊ ድርጅት ወይም ማህበር በግልጽ ጨረታው መሳተፍ

የምትፈልጉ፡-

  • በየመስኩ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ቲን-ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የቫት ተመዝጋቢነት ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የአቅራቢዎች የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ፣ በሲፕኦ ወይም በባንክ ስሊፕ (ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 1000268495812) ማስያዝ የሚችሉ፤ ተጫራቶች ሰነዱን ከሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሪከርድ እና ማህደር ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በሚቶ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመከፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ዶከመንት በሚገባ በመሙላት 01 /አንድ/ ኦሪጅናል እና 02 /ሁለት/ ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንት 01 /አንድ/ ኦሪጅናል እና 02 /ሁለት/ ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማስገባት እና በማሸግ የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ማህተም በመምታት እና የሚመለከተው የድርጅቱ ወይም የማህበሩ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ውከልና የተሰጠው አካል በመፈረም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለት 21 (ሀያ እንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 6፡00 ሰዓት ውስጥ ለጨረታው አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስገቢያው ቀን በተጠናቀቀበት ዕለት የጨረታ ሣጥኑ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን በ6፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው መከፈቻ ቀን እና ሰዓት ከደረሰ ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡

ማሳሰቢያ

1. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

2. አሸናፊ ድርጅት ወይም ማህበር የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት እና እቃ ነው፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያ ከተጠየቀው መጠን አሳንሶ የሚያስገባ ተጫራች የጨረታ መስፈርት ያላሟላ ተብሎ ውድቅ ይደረጋል፡፡

4. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ02 ወር /ስልሳ ቀን ነው፡፡

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በሥልጤ ዞን

 የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender