በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግሼ ወረዳ ውስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጥቅል ግዥ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4 የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት 5 ኮፒውተርና የኮፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ጎማና የጀነሬተር ባትሪዎች፣ ሎት 7 ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ሎት 8 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 9 የመኪና የመለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 10 የመኪና ዘይትና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡-01
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግሼ ወረዳ ውስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጥቅል ግዥ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4 የኮምፒውተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት 5 ኮፒውተርና የኮፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ጎማና የጀነሬተር ባትሪዎች፣ ሎት 7 ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ሎት 8 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 9 የመኪና የመለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 10 የመኪና ዘይትና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፤፡
3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
5. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፤
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ሎት 1 - የጽህፈት መሳሪያ ብር 50፤ ሎት 2 - የጽዳት እቃዎች ብር 100፤ ሎት 3 – ቋሚ የቢሮ እቃዎች ብር 80፤ ሎት 4 – የኮምፒውተርእና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች ብር 150፤ ሎት 5 – ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች ብር 150፤ ሎት 6 - የመኪና ጎማና የጀኔሬተር ባትሪዎች ብር 100፤ ሎት 7 - ቋሚ አላቂ እቃዎች ብር 80፤ ሎት 8 - የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ብር 150፤ ሎት 9 - የመኪና የመለዋወጫ እቃዎች ብር 200፤ ሎት 10 - የመኪና ዘይና ቅባቶች ብር 100 በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 መግዛትና ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንትበኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ከባንክ የተረጋገጠ Letter of credit ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የእለት ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች ለተጫረቱበት ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 1 ፐርሰንት ሲያሲዙ በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ማስገባት አለበቸው፡፡
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 06 በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
12. ጨረታውን ያሸነፈው እካል ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መግባት ይጠበቅበታል፡፡
13. ጨረታው በሎት በጥቅል ድምር መሆኑ ይታወቅ፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-1-19-13-14/ 033-8-99-01-02 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
17. ከላይ ያልተገለጸ ካለ በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
18. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
