Tender Detail

Tender Details

  • Company የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር
  • Address ቦሌ ሚካኤል ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline07 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price1500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-08 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማሰራት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተጠናቀቀ በመሆኑ የሁለተኛውን ምዕራፍ (Phase II) ለማሰራት ይፈልጋል።

የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር


 

በድጋሚ የወጣ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የቦሌ ደ/ም/ቅ/ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማሰራት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተጠናቀቀ በመሆኑ የሁለተኛውን ምዕራፍ (Phase II) ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ይህንኑ ሥራ ለማከናወን ፍላጎት፤ ችሎታና ልምድ እንዲሁም ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድና ሥራ ፈቃድ ያላችሁ እና በተመሳሳይ ሥራ ያላችሁን ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ደረጃ አምስት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ የሥራ ተቋራጮች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት አሥር ቀናት ውስጥ በደብሩ የመጠለያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የልማት ኮሚቴ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ከፍሎ በመውሰድ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለልማት ኮሚቴው ጽ/ቤት እንድታቀርቡ አንጋብዛለን።

ጨረታው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተወካዮች፣ የቦሌ እና ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተወካዮች፤ የደብሩ ሰበካ ጉባዔ፣ የልማት ኮሚቴ እና የአስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጫራቾች ወደም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በጨረታው ማስገቢያ የመጨረሻ ዕለት ማግስት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በሰበካ ጉባዔው አስተዳደር ጽ/ቤት ይከፈታል።

የሰበካ ጉባዔው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወደም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 

የደብሩ ሰበካ ጉባዔ አስተዳደር

 

Save Tender