Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፣ ኦሮሚያ፣ኢትዮጲያ, Phone: 0937526741
  • Website
  • Deadline14 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000.00
  • opening date2025-10-14 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Furniture , Stationery Materials , Electronics Materials

በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት * የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት እቃዎች ቋሚ እቃዎች፣ ፈርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፍ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የጃርሶ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት

* የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት እቃዎች ቋሚ እቃዎች፣ ፈርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሱትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሱ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ደጋብዛል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ስራ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ያጠናቀቁ ወይም ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከሊራንስ፣ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቶች የምትወዳደሩበትን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ጠቅላላ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በጥሬ ብር ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡

4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በሚደረገው ስምምነት መሰረት በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ከጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡

6. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

7. የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

8. ተጫራቶች ጨረታ በሚከፈትበት ቀን በጨረታው ውስጥ የተጠቀሱትን የኮምፒውተር ቀለም፣ የኮምፒውተር ወረቀት፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ እስከሪብቶ፣ ለናሙና አንዳንድ ፍሬ ማምጣት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የዝዙት እያንዳንዱ ሰነድ ገፅ ላይ ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ስለሚያቀርቡት እቃ የጥራት ደረጃ ጥራቱ ከሀገር ውስጥ ጥራት ደረጃ የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0937526741/0915020550 ደውለው ወይንም መሰሪያ ቤታችን ድረስ በመምጣት በጽሁፍም ሆነ በአካል በመገኘት መረዳት ይቻላል።

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ አሸናፊውን ለመለየት በጥቅል ወይም በእያንዳንዱ ዋጋ ላይ ተመስርቶ ሊያወዳድር ይችላል።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን

የጃርሶ ወረዳ ፍ/ቤት

Save Tender