የቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ ከዚህ የሚከተሉትን ዕቃዎችና ማሽኖች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
St. Mary's University (ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ ከዚህ የሚከተሉትን ዕቃዎችና ማሽኖች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ሀ. በጥቅም ላይ ያሉና የሚሠሩ ማሽኖች
- ማጠፊያ Folding Machine -1
- GTO/Offset ማተሚያ ማሽን -1
- Polar 90 መቁረጫ ማሽን -1
- መጠቅጠቂያ (Perforating Machine) -1
- ማበጠሪያ ማሽን -1
- Roller washer-1
- የከለር ሴፓረሽን (Color Separation) ማሽን -1 set
ሰ. የተወሠነ ብልሽት ያላቸው
- Three knife trimming machine-1
- Photocopy machine-1
- Copy printer E2-1
ማሣሰቢያ
- የማሽኖቹን ሁኔታ በዩኒቨርሲቲው ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት መመልከት የሚቻል ሲሆን ዝርዝሩን የያዘ የጨረታ ሰነድ በዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት የማይመለስ በብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተሳታፊዎች የተጫረቱበትን አጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በመክፈል ኦርጅናል ደረሰኙን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም አስከ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ያስገባሉ።
- ጨረታው መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርስቲው ዋና ጊቢ ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪ ክፍያቸውን ከፍለው ንብረቱን ያነሳሉ። ንብረቱን ማንሳት ካልቻለ በዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ገቢ ተደርጎ ጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል።
- የአሸናፊ ተጫራቾች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ሌሎች ተጫራቾች ያስያዙትን ገንዘብ የከፈሉበትን ኦርጅናል ደረሰኝ በማቅረብ ተመሳሽ ማድረግ ይችላሉ።
- ተቋሙ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 550 31 93 ደደውሉ።
