የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር የ2017 በጀት ዓመትን የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/ እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር
በድጋሚ የወጣ
የውጭ ኦዲተር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት መጋቢት 04/2013 በመቋቋም ባለፉት ዓመታት ለአባላቱ የቁጠባ እና የብድር አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። በመሆኑም የ2017 በጀት ዓመትን የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/ እውቅና የተሰጣቸውን የኦዲት ተቋማትን/ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾ/የኦዲት ድርጅቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
ፍላጎት ያላችሁ የኦዲት ድርጅቶች ፡-
- ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ (Technical proposal)
- የፋይናንስ መነሻ ሀሳብ (Financial proposal)
- በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርትፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የግብር ከፋይነት ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የማህበሩን የግዥ ሂደት የተከተለና በሀገሪቱ የግዥ ህግ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- በኢትዮጵያ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ /AABE/ እውቅና ሰርትፊኬት መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ነጋዴዎች አ/ማ ህንፃ 23 ፎቅ ዘወትር በቢሮ የስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋውን 2 በመቶ በሲፒኦ /በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ/ ከፋይናንስ ፖስታ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለተጫራቾች ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ (Technical proposal) የሚሆናቸውን ዝርዝር ቢጋር (TOR) የያዘ ሰነድ በማህበሩ የፋይናንስ እና ግዥ ክፍል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት የሚቆይ/ ከሰኞ አርብ ከጧቱ 2:30 እስከ 11:30 እና ቅዳሜ ጧት ከ2፡30 እስከ 6፡30/ ሆኖ ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ ሰነዳቸውን ካስገቡ በኋላ በእለቱ 10ኛው ቀን ከሰአት በኋላ 11፡30 ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የሥራ ቀን ላይ ጧት በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው መክፈቻ 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ስልክ 0115571399 ወይም 0948051115 ወይም 0911997050
ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላ/የተ/መ/የህብረት ስራ ማህበር
አዲስ አበባ
