ሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የምግብ አቅርቦት ግዥ ለ45 ስፖርተኞች የሚሆን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Sidama Football Federation (የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን)
ሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ድጋሚ የወጣ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን
በ2018 በጀት ዓመት የምግብ አቅርቦት ግዥ ለ45 ስፖርተኞች የሚሆን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች:-
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50.000 (ሀምሳ ሺ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ::
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ቴከኒካል እና አንድ ፋይናሻል መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: 16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተዘግቶ በማግስቱ በሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልከ ቁጥር ማስፈር አለባቸው::
7. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት/ መጠን/ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ / ለመጨመር / መብቱ የተጠበቀ ነው::
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የምግብ⁄ዕቃ አይነት /መ/ቤቱ ባቀረበው በሜኑ ዝርዝር መሰረት
ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት ::
9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0462216730 /0916155930 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:: የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት ፊት ለፊት
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን
