Tender Detail

Tender Details


የቦርቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል 1. የጽሕፈት መሣሪያ በጥቅል ለመግዛትና 2. በአዳራሽ ውስጥ ለመቀመጥ የሚሆን ወንበር ደረጃውን የጠበቀ ሲቀመጥ የሚከፈት ሲነሣ በራሱ የሚዘጋ ተጣጣፊ ወንበር ግዥ ለመፈፀም ማቅረብ ከሚችሉ ሕጋዊ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የቦርቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የቦርቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል 1. የጽሕፈት መሣሪያ በጥቅል ለመግዛትና 2. በአዳራሽ ውስጥ ለመቀመጥ የሚሆን ወንበር ደረጃውን የጠበቀ ሲቀመጥ የሚከፈት ሲነሣ በራሱ የሚዘጋ ተጣጣፊ ወንበር ግዥ ለመፈፀም ማቅረብ ከሚችሉ ሕጋዊ ነጋዴዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ መስክ ሥራ የተሰማራችሁት ማሟላት የሚገባችሁ መስፈርቶች፡-

  1. የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የነበሩ፤
  3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  4. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  5. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  6. ጥራት ያለውን ዕቃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በዕቃው ላይ የጥራት ጉድለት ቢገኝ በራሳቸው ኪሳራ መልሰው ጥራት ያለውን ዕቃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ በራሱ ትራንስፖርት አስከ ቦርቻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  9. CPO በባንክ የተረጋገጠ ለጽሕፈት መሳሪያ 10,000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. CPO በባንክ የተረጋገጠ አዳራሽ ወንበር 100,000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ለጽሕፈት መሳሪያ ተወዳዳሪዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ለማጣራት እንዲረዳን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የወቅቱን ዋጋ ያላገናዘበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ከጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  14. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ከቅድመ ክፍያ መጠን የሚሆን ከባንክ ጋራቲት ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  15. የአዳራሽ ወንበር አሸናፊ የሚሆነው በራሱ ባለሙያ አቅርቦ ወንበሩን ገጣጥሞ ያስረክባል፡፡

ከ1-5 ድረሰ ያሉት መስፈርቶችን የምታሟሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቦርቻ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ቦርቻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ ሠነዱን ትወስዱና የተጠየቃችሁን መረጃና የመሸጫ ዋጋ ሞልታችሁ በፖስታ በማሸግ እንድትመዘገቡ እየገለጽን የታሸገው ፖስታ በመ/ቤት ውስጥ ለዚህ ሥራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

ሣጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በ16ኛው የሥራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ዕለት ልክ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የታሸገው ፖስታ ይከፈታል፡፡

ጨረታው ተከፍቶ የሚቆይበት ጊዜ እስከ 60 የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-16-07-55-31/ 09-16-48-56-58

 

የቦርቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

Save Tender