Tender Detail

Tender Details


የቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ ግዥዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Grand Bishoftu Hospital (ቢሾፍቱ ሆስፒታል)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ ግዥዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • የመድሀኒት፣ ሰፕላይ፣ ሪኤጀንት እና ህክምና መሳሪያ
  • የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ (stationery)፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች እና የውሃ መስመር መጠገኛ ዕቃዎች /የቧንባ መለዋወጫ እቃ/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  1. በቅርብ በ2017 የታደሰ ከስራው ጋር የተዛመደ የንግድ እና የሙያ ፍቃድ እንዲሁም Tin Number ያለው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ለጽዳት እቃዎች፤ የፅህፈት መሳሪያ (stationery) የኤሌክትሪክ እቃዎች እና የውሃ መስመር መጠገኛ እቃዎች /የቧንቧ መለዋወጫ እቃ/ በእያንዳንዱ 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) ለመድሃኒት፤ ሰፕላይ፤ ሪኤጀንት እና ህክምና መሳሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በሆስፒታሉ ስም ማስያዝ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዋጋ በማወዳደር የሚያልፉ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት በታሸገበት ፖስታ ወይም ኤንቨሎፕ በሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ የጨረታ ሰነድ ጋር ያለውን መስፈርት አሟልቶ የተገኘ በኃላፊው ስምና ፊርማ ማህተም ያለው መሆን አለበት።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 47 ለእያንዳንዱ ሎት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ሎት 1 የመድሃኒት፤ ሎት 2 ሰፕላይ፣ ሎት 3 ሪኤጀንት፤ ሎት 4 ህክምና መሳሪያ፤ ሎት 5 የፅዳት እቃዎች ፤ ሎት 6 የፅህፈት መሳሪያ (stationery)፤ ሎት 7 የኤሌክትሪክ እቃዎችና ሎት 8 የውሃ መስመር መጠገኛ እቃዎች /የቧንቧ መለዋወጫ እቃ/
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በአስራ አንደኛ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሆስፒታሉ ላይብረሪ ይከፈታል፡፡
  8. ሆስፒታሉ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 437 1271 / 011 433 81 87 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የቢሾፍቱ ሆስፒታል

 

Save Tender