Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ሰብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች ፣ ቋሚ ዕቃዎች እና ሌሎችም በ1ኛ ዙር ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ሰብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች ፣ ቋሚ ዕቃዎች እና ሌሎችም በ1ኛ ዙር ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች የተሰማበት የስራ መስከ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ TIN No የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ዋጋው ቫት ጨምሮ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ዋጋውን ሞልተው ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ በቀበና ት/ቤት ስም

  • ለደንብ ልብስ ተጫራች:- ብር 12,000.00 (አስራ ሁለት ሺህ ብር ብቻ)
  • ለአላቂ የቢሮ እቃዎችና ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች ተጫራች:-ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
  • ለህትመት አገልግሎት ተጫራች፡-ብር 3,600.00 (ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ብርብቻ)
  • ለአላቂ የህከምና እቃዎች ተጫራች፡- ብር1,000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሌሎች አላቂ እቃዎች ተጫራቾ፡-ብር 13,500.00(አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)
  • ለፕላንት፣ በማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዢያ ተጫራች:-ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
  • ለህንፃ፣ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዢያ ተጫራቾ:-ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋርአያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200(ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።

5. አሸናፊው ተጫራቾች ውል ሲዋዋሉ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ ጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም:: በጨረታ ስነድ 4.6 እና 9 የተቀመጡት ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሟልቶ ያላቀረበ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም::

7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ዕቃ ምርት ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚ መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም::

10. ት/ቤቱ ሰነዱ ላይ ካሰፈራቸው ውጪ ምንም ዓይነት የዋጋ፣የውድድር እና የቴከኖሎጂ አማራጮችን አይቀበልም::

11. መስረያ ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

12. ሰነዱ ላይ ዋጋ ሞልተው ሲያስገቡ የሚወዳደሩበት ሎት መጨረሻ ላይ የእቃዎቹ ጠቅላላ ድምር ዋጋ ይገለፅ።

አድራሻ:- ከቀበና አደባባይ ወደ ጀርመን ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ቤላ ገስት ሀውስ ጀርባ ላይ::

ስልክ:- 011 6 58 42 54/ 011 1 23 48 90

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender