በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት ለሴከተር መ/ቤቶች የ ጽ/መሳሪያና የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ /ሞተር ሳይክል/፣ ግንባታ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት ለሴከተር መ/ቤቶች የ ጽ/መሳሪያና የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪ /ሞተር ሳይክል/፣ ግንባታ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1ኛ ሎትı ጽ/መሳሪያ፣የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች
2ኛ ሎት2 ኤሌክትሮኒከስ /ኮምፒውተር፣ ፒርንተር፣ ኮፒ ማሽን እና ተዘማች ዕቃዎች/
3ኛ ሎት3 ተሽከርካሪ/ሞተር ሳይከል/
4ኛ ሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች ቆርቆሮ ፣ ሰሚንቶ ፣ ሚስማርና ተዘማች ዕቃዎች
የተጫራቾች መስፈርት:-
1) በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀትያለው፤
2) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ተመዝጋቢ PUP
3) የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት ያለው፤የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
4) የጨረታማስከበሪያ /BID BOND/ ለእያንዳንዱ ሎት 30,000.00/ሰላሳ ሺህ ብር/ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የከፊያ ማዘዣ /cpo/ ወይም በጥሬገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክረድት ከተክኒካል ኦርጂናል ጨረታ ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።
5) የተጫረቱትን ዕቃ እስከ ወረዳው ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የመኪና ኪራይና ጫኝ አውራጅ ወጪ በመሸፈን እስከ ቦረዳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ማስረከብ የሚችል።
6) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15/ አስራ አምስት/ ቀናት ሲሆን የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ለመግዛት ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመከፈል ደረሰኝ በመያዝ ሰነዱን ከፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ የሚችል።
7) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሳጥን ክፍት በመሆኑ ተጫራቾች በፋ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና በ16ኛው ቀን በፋ/ጽ/ቤት ግዥን ብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥን ይታሸጋል። በዕለቱ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይበተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ለውድድሩ ስቀርብ ኦርጅናል ሙሉ የጨረታ ዶከመንት በእጁ ይዘው መቅረብና ናሙና ስፈለግ ይዘው መቅረብ ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ:-
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከወላይታ ሶዶ ከተማ እስከ ቦረዳ ወረዳ ዘፍኔ ከተማ ድረስ ያለው ርቀት 71ኪ.ሜ
- ከዞኑ ዋና ከተማ አ/ምንጭ እስከ ቦረዳ ዘፍኔ ከተማ ድረስ ያለው ርቀት 94 ኪ.ሜ
- ከአስፋልት እስከ ቦረዳ ወረዳ ዘፍኔ ከተማ ድረስ ያለው ርቀት 24 ኪ.ሜ
- ለበለጠ መረጃ ስልከ 0948226764
በጋሞ ዞን የቦረዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
