ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ባለአንድ አባል ኃ.የተ.የግ.ማ በሪል እስቴት ዘርፍ በአፓርትመንት ቤቶች ግንባታ ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ድርጅታችን የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የሂሳብ ማጠቃለያ ሪፖርትን በተመሰከረለት ሂሳብ አዋቂ ድርጅት ማስመርመር ይፈልጋል።
Deluxe Properties (ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ባለአንድ አባል ኃ.የተ.የግ.ማ)
የሂሳብ ኦዲት አገልግሎት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ባለአንድ አባል ኃ.የተ.የግ.ማ በሪል እስቴት ዘርፍ በአፓርትመንት ቤቶች ግንባታ ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ድርጅታችን የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የሂሳብ ማጠቃለያ ሪፖርትን በተመሰከረለት ሂሳብ አዋቂ ድርጅት ማስመርመር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟላ የተመስከረለት የሂሳብ አዋቂ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል። በዚሁ መሠረት፡-
- የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂ የሙያ ፍቃድ ወይም HAABE ስርቲፋይድ ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ
- በዋና ኦዲተርነት የተመዘገበበት ህጋዊ መረጃ ያለው
- በሪልእስቴት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ተቋማት ኦዲቲ ማድረጉን የሚያሳይማስረጃ ማቅረብ የሚችል
ተጫራቾች የድርጅታቸውን አቋም የሚገልጽ ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ታክስን ጨምሮ የሚያስከፍሉትን አገልግሎት ዋጋ ፋይኔንሻል ፕሮፖዛል እንዲሁም የሂሳብ ምርመራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን ቀን /ግዜ በመጥቀስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በድርጅታን ዋ/መ/ቤት በአካል ማቅረብ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታው የሚያስፈልገውን ዝርዝር መረጃ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በድርጅቱ ዋ/መ/ቤት በአካል ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ ፕላቲንየም ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 ላይ ይገኛል።
የበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥር +251 0911- 89 27 16/+251-0913-71 30 77 በመደወል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
