በአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
በአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፡-
ሎት 1. የደንብ ልብስ፣
ሎት 2. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣
ሎት 4. የህትመት እቃዎች
ሎት 5. የተሽከርካሪ ዕቃዎች፣
ሎት 6. አላቂ የአይቲ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና /Tin No/ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-10፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፋይናንሺያል ሰነድ እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ መፈረም እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባለው ቀን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-22-45-04-40/09-10-70-49-72 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ በር 3 ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 31 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።
አሽ/ተሸ/ፈ/ቀ/ ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
