Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462200072
  • Website
  • Deadline10 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityለኤሌክትሮኒክስ ጨረታ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲሁም ለፈርኒቸር ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Electronics Materials

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሎት1. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና በሎት2. ፈርኒቸር ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ግልፅ 01/2018

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሎት1. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና በሎት2. ፈርኒቸር ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መሃተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ላይ በተጠቀሱት ለመወዳደር በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. በገቢዎች ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. ማንኛውም ተጫራች የኤሌክትሮኒክስ ጨረታ ማስከበሪያውን 10,000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲሁም ለፈርኒቸር ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በቢሮው ስም በማሰራት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ /cpo/ ማስያዝ አለበት፡፡
  4. አሸናፊ ተጫራች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
  5. ተጫራች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ የጨረታ ሠነዱን ንግድ ፍቃዳቸውን በማሳየት 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲዳማ /ክልል/ፐብ/ሰ/የሰ/ሃ/ል/ቢሮ ስም በተከፈተዉ አካውንት ቁጥር 1000340576997 በማስገባት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና 2 ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና 2 ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16 /አስራ ስድስተኛው/ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
  7. በአስራ ስድስተኛው ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ሕጋው ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በሮ ቁጥር 23 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮ ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን ይገልጻል፡፡
  9. ይህ ጨረታ ከተሞላበት ቀን ጀምሮ ዋጋ የሚፀናበትን ከ60 ቀናት የግዜ ገደብ በታች መስጠት የለበትም፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከሰባት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውሉን መፈረም ይኖርበታል፡፡
  11. አሸናፈው ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እያንዳንዱን እቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 ቀናት ወስጥ በራሱ ወጪ በማቅረብ በተፈለገውና በተጠየቀው ስፔስፍኬሽን መሆኑን በባለሙያ ከተጣራ በኋላ ማስረከብ አለበት፡፡
  12. አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደጠናቀቀ ክፍያው ወዲያውኑ በቼክ ይከፈላል፡፡
  13. አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ አለመፈፀሙ ሲረጋገጥ በውል ግዴታው መሠረት በህግ አግባብ ይጠየቃል፡፡
  14. ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት ዳይሬክቶሬት የስልክ ቁጥር 0462200072

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

 

Save Tender