Tender Detail

Tender Details


በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 9Gu የቢሮ እቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 9Gu የቢሮ እቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታው መስፈርቶች፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከጃርደግ ጃርቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ለእያንዳንዱ ሰነድ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዓይነቱ ለይቶ አርጂናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸወ። የዕቃ ሞደል ማቅረብ /sample /እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማውንና ህጋዊ ማህተሙን በመምታት የዋጋ ማቅረቢያውን ከቫት ጋር በመሙላት የመስሪያ ቤቱን አድራሻ፣ ስልክ ቁጥርን በመፃፍ ማኅተም መተው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች አሸናፊ ለሆኑባቸው የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) የሚያስረከበው የተገጠመውን ነው፡፡
  7. ተጫራቹ ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለእያንዳንዱ የሰነድ ዓይነት ለየብቻቸው በባንክ በተመሰከረ ቼክ 2% ከጠቅላላ ድምር ከሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
  8. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ባሸነፉባቸው እቃዎች መ/ቤቱ አሸናፊ መሆናቸውን ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በጽ/ቤቱ ቀርበው ውል ካልገቡና ለሚገባቸው እቃዎች በሲፒኦ / 10% ካላስያዘ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ብር በመውረስ ጽ/ቤቱ አማራጭ መፈለግ መብት አለው፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉዋቸውን እቃዎች በመ/ቤታችን መጋዘን የማስረከብ ግደታ አለባቸው፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. መ/ቤቱ የሚገዛቸው እቃዎች ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥና ከጨረታ መውጣት አይችሉም።
  13. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ15 /አስራ አምስት /ተከታታይ የስራ ቀናት እና የስራ ሰዓት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እና በ15 /አስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 11፡25 ሰዓት ገቢ ሆኖ በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው/ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ አስራ ስድስተኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ጨረታው ፀንተው የሚቆየው ለ60 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  15. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የምንረከበው የተሞላውን እና በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

 

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender