በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ የ2018 በጀት ዓመት የሚከተሉትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ |
|
1 |
1 |
አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች |
3,000 |
|
2 |
2 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
3,000 |
|
3 |
3 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
10,000 |
|
4 |
4 |
የህትመት ውጤቶች |
2,000 |
|
5 |
5 |
የደንብ ልብስ |
3,000 |
|
6 |
6 |
የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች |
20,000 |
|
7 |
7 |
መሰረተ ልማት እቃዎች ግዥ ጥገና (አድሳት) |
3,500 |
|
8 |
8 |
የአልትራሳውንድ አገልግሎት |
|
|
9 |
9 |
የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች እድሳትና ጥገና አገልግሎት |
5,000 |
|
10 |
10 |
ለተቋሙ ሠራተኞች የካፍቴሪያ አገልግሎት |
|
ተጨራቾች፡-
11. በዘርፉ ከተሰማሩበት ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
12. በድረ ገጽ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው በአላይን የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
13. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀትእና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
14. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200 ብርበመከፈል የጨረታ ሰነድ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
15. ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 409 ድረስ በመምጣት ሙሉ የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
16. አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚያመርቱት ምርት ብቻ ከከፍያ ነፃ ሰነድ ይወስዳሉ፡፡
17. ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
18. ተጫራቾች ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
19. ተጫራቶች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎት ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
20. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ወጪ የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
21. ጤና ጣቢያው በጨረታ ሰነድ ከፍል 6 ላይ ከተጠቀሰው መጠን 20% ድረስ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
22. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ነው፡፡
23. ተጫራቾቹ የጨረታውን ማስከበሪያ ሲፒኦ በየሎቱ ለየብቻ ማሰራት አለባቸው፡፡
24. ተጫራቾች ሲፒአ ኮፒ እና ኦርጅናል ይዞ መምጣት አለባቸው፡፡
25. ተጫራቾች መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ላይ በየአንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተብምእና ፊርማ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
26. አነስተኛና ጥቃቅን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም በውድድሩ ካሸነፊ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከተደራጁበት ወረዳ ደብዳቤ ማምጣት አለባቸው፡፡
27. ተወካዮች ውል ለመዋዋልና ለተለያየ አገልግሎት ሲመጡ የውክልና ደብዳቤ ይዘው መምጣት አለባቸው::
28. ጤና ጣቢያው ተጫራቾች ውል ተዋውለው ለሚያቀርቡት እቃ ላይ እስከ 6ወር ድረስ በተመሳሳይ ዋጋ 25 በመቶ ተጨማሪ ግዥ ማከናወን ይችላል፡፡
29 መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለሕከምናመሣሪያ ለምትወዳደሩ ድርጅቶች ሰነድ በምታሰገቡበትወቅት በሰም በታሸገ ፖስታ ከተቋሙ የምትወስዱት Specification እና ስለማሽኑ የሚገልጽ (Catalog) አንድ ላይ ያስገቡ፡፡
አድራሻ፡- አ/ከ/ከ/ከተማ ወረዳ 1ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታው መርካቶ አሜሪካን ግቢ ኡራጎ ሕንፃ ጀርባ
የመን ኮሚኒቲ ት/ቤት አጠገብ፡፡ ስልክ ቁጥር 011273
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ
