በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የግርጃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ለቢሮወች አላቅና የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፡ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ ተሽክርካሪ ሞተሮች፣ የመኪና ጎማ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ጄኔሬተሮችን ለ2018 የበጀት ዓመት የሚያቀርብ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የግርጃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የግርጃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ለቢሮወች አላቅና የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፡ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ ተሽክርካሪ ሞተሮች፣ የመኪና ጎማ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ጄኔሬተሮችን ለ2018 የበጀት ዓመት የሚያቀርብ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛውም በዚህ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ አቅራቢ በውድድሩ ላይ እንዲካፈል እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች መስፈርቶች/ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እና መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ኦሪጅናል ሰነዱ ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት በመክፈል ከግርጃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ የተመሰከረለት ቼከ/CPO/ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
4. አሸናፈው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ወዲያውኑ ለተሸናፊዎች የሚመለስ ይሆናል።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታ አይነቱን በግልጽ በመፃፍ ኮፒና ኦሪጅናሉን እስከ 3/2/2018 ዓ.ም እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በግርጃ ወረዳ ዝጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደርከፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት አለበት።
6. ጨረታው 3/2/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በግርጃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች እንዲያቀርብ ከመ/ቤቱ በጽሁፍ ከታዘዘበት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
8. የጨረታው አሸናፊ በግልፅ ማስታወቂያ /በደብዳቤ/ ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለአሸነፈባቸው ዕቃዎች ዋጋ 10 % የጨረታ ውል ማስከበሪያ በኢንሹራንስ /ጋራንቲ/ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ አስይዞ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ይህንን ባይፈጽሙ መ/ቤቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የያዘውን ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ያደርገዋል።
9. እንዲቀረበ የሚታዘዙትን ዕቃዎች ድርጅቱ በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማስረከብ አለበት።
10. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ወከሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና ኦሪጅናል የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት።
11. የጨረታው የመግባቢያ ቋንቋ ኦሮሚኛ ነው።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ሞባይል ቁጥር ፡- 09-10-17-25-31/ 09-26-22-77-38/ 09-75-97-61-72
በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የግርጃ
ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
