በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
- የቧንቧ ውሃ ዝርጋታ ዕቃዎች፣ የቧንቧ መፍቻዎች
- ፓምፕ (pump)፣ የውሃ ቆጣሪ /water meter
- የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች
- የደንብ ልብሶች፣ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ባጃጅ
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ።
- የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- ቫት እና ቲን (TIN) ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ በጥንቃቄ ታሽገው ፋይናንሻል /financial/ አንድ (1) ኦርጅናል ቴክኒካል (technical) አንድ (1) ኦርጅናል፣ (2) ኮፒ ፋይናንሻል (financial) እና (2) ኮፒ ቴክኒካል /technical/ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ እንዲሁም በፖስታ ላይ ማህተም በመምታት በሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል። ሰነዱ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው የሚሞላው በነጠላ ዋጋ ነው።
- በተጫራቾች ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ግልጽና አጠራጣሪ ባልሆነ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ባልሆነ ጽሑፍ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም የሃሳብም ሆነ የዋጋ ማሻሻያ በማቅረብ ከጨረታው ውጪ መሆን አይቻልም።
- የሚቀርቡት ዕቃዎች 1ኛ ደረጃ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ለማሸነፍ ብሎ ዕቃውን የማይመጥን ያልሆነ ዋጋ ሞልቶ ወይም ሰጥቶ እቃው ሲቀርብ 2ኛ ደረጃ ከሆነ የማንቀበል መሆኑን አስቀድመን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 700 ብር እያንዳንዱ ዝርዝር ላይ በመክፈል ከሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ ድርጅት በሂሳብ እና ፋይናንስ አስተዳደር የስራ ሂደት ክፍል ቀርበው ማግኘት (መግዛት) የሚችሉ መሆኑን።
- ማንኛም ተጫራች መ/ቤቱ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል። ባላቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኋላ በመጀመሪያ የሥራ ቀን በ3:30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ሞጆ ከተማ ውሃ አገልግሎት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ 60,000 (ስልሳ ሺ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ እና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው ጽሕፈት ቤት የዋስትና ደብዳቤ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት ጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ እና በስልክ እንደተገለጸ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊዉን የጨረታ ውል ሞጆ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጋር መፈራረም አለበት።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።
- መሥሪያ ቤቱ ከሚደረገው የግዥ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በፖስታውና በሰነዱ ላይ ህጋዊ ማህተም ፤ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
ለበለጠ መረጃ የሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ስልክ ቁጥር 0221161166 / 0221161127
የሞጆ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
