Tender Detail

Tender Details


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 የቢሮ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች እና የፅዳት እቃዎች ግዥ
  • ሎት 2. የወለል ምንጣፍ እና የመጋረጃ ግዥ

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 ድረስ ብቻ ለዘህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  5. ከላይ በሎት ቁጥር 1-2 የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ 90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለአንዳንዱ ሎት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይቻላል።
  9. አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለተጠየቁ እቃዎች ማቅረብ አለባቸው።
  11. ዝርዝር የዕቃዎቹ ናሙና በጨረታ ሰነድ ላይ ቀርበዋል፡፡
  12. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-7002/3

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ሀዋሳ

 

Save Tender