በስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የት/ት ዘመን ለሚያስተምራቸው እስከ 480 ለሚደርሱ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል የባልትና ዕቃዎች፣ ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዳቦ፣ የጤፍ ዱቄት የማገዶ እንጨት እና ስጋ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የት/ት ዘመን ለሚያስተምራቸው እስከ 480 ለሚደርሱ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል የባልትና ዕቃዎች፣ ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዳቦ፣ የጤፍ ዱቄት የማገዶ እንጨት እና ስጋ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል ፡፡
የዕቃዎቹ ዝርዝር የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO መጠን
-
ለጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ እና የባልትና ዕቃዎች.. 5000.00
-
ለዳቦ ብር 2000.00
-
ለጤፍ ዱቄት -ብር 5000.00
-
ጥሬ ስጋ-- -ብር 3000.00
-
ለማገዶ እንጨት- ብር 3000.00
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-
-
በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፍቃድና የስራ ልምድ ያላቸው፡፡
-
የዘመኑን የሥራ ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ፡፡
-
የቲን ቁጥር ያላቸው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO በሚወዳደሩበት ዕቃ በተጠየቀው መጠን ማስያዝ አለባቸው፡፡
-
አሸናፊ የሆነ ድርጅት ንብረቱን እስከ ሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በውሉ መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡
-
ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ከሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
-
ከአንድ በላይ በሆኑ ዕቃዎች የሚወዳደር አቅራቢ በእያንዳንዱ በሚወዳደርባቸው ዕቃዎች የተጠየቀውን CPO ማስያዝ ይኖርበታል
-
ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ15ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 9፡30 በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን:: ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሳምንት መጨረሻ ቀናት ወይንም የበአል ቀናት ላይ ካረፈ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በሰም የታሸገ ፖስታ ሆኖ ስማቸውን ፣ ፍርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
-
የሚቀርበው ሰነድ በዋና እና በኮፒ መሆን ይኖርበታል፡፡
-
ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
-
ተጫራቾች ሆኑ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት የሚያስቀራው ነገር ሊኖር አይችልም፡፡
-
ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ መጀመር የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710462 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በስልጤ ልማት ማህበር የሀይረንዚ ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
