ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ የህፃናትና የወጣቶች እንዲሁም የማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 500 የተማሪ ቦርሳ ( 152 የመዋዕለ ህፃናት እንዲሁም 348 ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ የህፃናትና የወጣቶች እንዲሁም የማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 500 የተማሪ ቦርሳ ( 152 የመዋዕለ ህፃናት እንዲሁም 348 ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አገልግሎት የሚውል) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ድርጅቱ የሚያቀርበውን ቦርሳ ናሙና (ሳምፕል) ፅህፈት ቤቱ ድረስ በመምጣት በመመልከት ማቅረብ የሚችልና ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች እና አስፈላጊ ሰነዶችን የሚያሟሉ ከታች በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነድን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
መስፈርቶች/ሰነዶች
-
በጨረታው ለመወዳደር የሚያበቃቸው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ሥራ የምዝገባ ፈቃድ
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስከር ወረቀት
-
አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንክ የክፍያ ትእዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ጨረታውን አሸናፊ ድርጅት የተጠየቁትን ግብአቶች (የተማሪዎች ቦርሳ) ውል ከተፈራረመበት እለት ጀምሮ በ3 ቀን ውስጥ ማስረከብ የሚችል መሆን ይገባዋል፡፡ እንዲሁም በራሱ ትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በ5ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው በተዘጋበት እለት 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-157-51-25 ወይም 011-157-08-65 CPO የሚሰራበት Chora for Children and Family Development አድራሻ፡- ሰሜን መዘጋጃ ከፍ ብሎ ድልበር ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት
ጮራ ለሕፃናትና ቤተሰብ ልማት
