የጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ኮሌጁ ከሆፕ ኢንተርኘራይዝ ድጋፍ አጫጭር ስልጠና * አገልግሎት የሚውል የጋርመንት፣ የኮንስትራክሽንና የግብርና ስልጠና ዕቃዎች በሃገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
Jinka Polytechnic College (የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ኮሌጁ ከሆፕ ኢንተርኘራይዝ ድጋፍ አጫጭር ስልጠና * አገልግሎት የሚውል የጋርመንት፣ የኮንስትራክሽንና የግብርና ስልጠና ዕቃዎች በሃገር አቀፍ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ በጨረታው ላይ _ ለመወዳደር/ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች፤
በዚሁ መሠረት፡-
-
አግባብነት ያለው የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
-
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ በጨረታ ለመሣተፍ የሚችሉበት ከሚመለከተው አካል ለ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ማስረጃ እና በፋ/ኢ/ል/ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ደብዳቤ ፎቶ ኮፒ በመያዝና የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ ብቻ በጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ የባንክ አካውንት ቁጥር 1000040809299 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ በመያዝ በጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 203 መጥተው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 5000(አምስት ሺህ ብር) በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ አልያም በጥሬ ገንዘብ በማዘጋጀት የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቪሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፁት በአንዱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ፡፡
-
የመጓጓዣ ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ሲሆን እስከ ጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ንብረት ከፍል ዕቃውን ገቢ ማድረግ የሚችል፣.
-
ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልጽ በመሙላት በማህተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣.
-
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ያበቃና የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 203 በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፤
-
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጂ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ
