Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ
  • Address ፊንፊኔ ሳርቤት (የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ) ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118331547
  • Website
  • Deadline30 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price50.00
  • Bid Security10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-30 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Cleaning And Janitorial Equipment

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የፅዳት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-ኦከልቤቢ 1/2018

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የፅዳት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ለተጠየቀው አገልግሎት የዕቃ ግዢ የዘርፉን ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ በፌዴራል ወይም በክልል የ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መስሪያ ቤት በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቀጥር (Tax payer registration No) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸውና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳርቤት በሚገኘው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ 4ኛ ፎቅ የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት በአካል በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በሚጫረቱበት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖሰታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማሰታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በጠዋቱ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው እለት በጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ስም ከታወቀ ባንከ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲ.ፒ.ኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር በተቀመጠው ቀን ገደብ ሥራዎቹን ማጠናቀ አለበት።
  8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118331547

አድራሻ፡- ፊንፊኔ ሳርቤት (የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ)

 

የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ

 

Save Tender