ኩባንያችን ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግ/ኩ ከጅቡቲ ታጁራ ወደብ ወደ ሰሜን ሸዋ ለሚ ከተማ እንሳሮ ወረዳ ለሚ ፋብሪካ የድንጋይ ከሰል ትራንስፖርት ለማድረግ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች በጨረታ አወዳድሮ መዋዋል ይፈልጋል፡፡
LEMI NATIONAL CEMENT PLC (ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግ/ኩ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግ/ኩ ከጅቡቲ ታጁራ ወደብ ወደ ሰሜን ሸዋ ለሚ ከተማ እንሳሮ ወረዳ ለሚ ፋብሪካ የድንጋይ ከሰል ትራንስፖርት ለማድረግ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች በጨረታ አወዳድሮ መዋዋል ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን የትራንስፖርት አገልግሎት የአንዱን ሜቶን ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 1ኛ ፎቅ አ.አ ስልክ፡- 0960367136/0914734193 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም 03/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጨረታው ተዘግቶ 03/01/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ኃ/የተ/ግ/ማህበር ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ:-
ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ
