በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን LOT1. የደንብ ልብስ ሱፍ /ሙሉ ልብስ/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን -
LOT1. የደንብ ልብስ ሱፍ /ሙሉ ልብስ/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ እና የታደሰ የ2017 ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡
- ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 19% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ10 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ማስገባት እና ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Deviation) አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬከተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
