Tender Detail

Tender Details


በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች

2.የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

3.የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ የመማሪያ መሳሪዎችን

4.የሰራተኞች የደንብ ልብስ

5.የመኪና እና የሞተር ጎማዎች

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም የ2018 ዒ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱና TIN NO እንዲሁም የምዝገባ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ ላይ እንደሆነ በሰነዶቻችሁ ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም (Brand Name) እና የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።

በነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል።

5. ጨረታው ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 1/03/2017 ጀምሮ እስከ 16 /1/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ) ብር በመከፈል የጨረታ ሰንዱን ከገደብ ሀሳሳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ከነቫት መሆንና አለመሆኑን በግልጽ በመጥቀስና የድርጅታችሁን ማህተምና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በስራ ሰዓት በቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሰነድ 5000 ብር በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ብር በገደብ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸው እና በአስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፈው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ገደብ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ማለትም 19/01/2018 የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰአት ተዘግቶ በዛው እለት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤታችን ቢሮ ቁጥር3 ይከፈታል።ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም የበእል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የሚከፈት ይሆናል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12.አሸናፊ ተጫራቶች የአሸነፉትን እቃዎች አጠቃላይ ዋጋውን 10% ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

13.ተጫራቾች VAT ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅበቸል።

14.የደንብ ልብስ ሲቀርብ የምታቀርቡትን አይነት ናሙና መቅረብ ይኖርበታል።

15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912253576/0913819389 መደወል ይችላሉ።

በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ መስተዳድር የገደብ ሀላꬃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

Save Tender