Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2/አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን እና አገልግሎት በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2/አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ፡-001/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2/አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን እና አገልግሎት በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት

የዕቃው አይነት

የጨረታ ማክበሪያ ዋስትና የብር መጠን 2%

1

አላቂ የቢሮ ፅህፈት እቃዎች

7,950.00

2

አላቂ የት/ት መሳሪያዎች

7,950.00

3

የጽዳት ዕቃዎች

16,200.00

4

የደንብ ልብስ

15,000.00

5

የተለያዩ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች

22,000.00

6

የጥገና እቃዎች

19,700.00

7

የተለያዩ የህትመት ሥራዎች

4,000.00

8

ለፎቶ ኮፒ እና ፕሪንተር ማሽነሪ ጥገና እና ሰርቪስ

2,640.00

9

የመስተንግዶ ውሃ/ቆሉ ግዥ

1,377.50

10

የጭነት አገልግሎት

5000.00

 

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር www. ppa.Jov ውስጥ የተመዘገቡ

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴከኒከ ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል ኮፒ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር አንድ አርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ አይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የመጫረቻ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በት/ቤቱ ላይብረሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡ 30 ላይ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡:

 

4. የመጫረቻ ሰነድ (SBD) በነጋዴ መሞላት ያለበት ቦታ በትከከል መሞላት ይኖርበታል:: በተጨማሪም የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ መኖር አለበት :: ያልተሟላ ሰነድ ከሆነ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳውቃለን።

5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሠኞ - አርብ አጠቃላይ የሎት መግዣ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

6. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኃላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% ዋጋው በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኃላ ወይም የጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኃላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው የውል ማስከበሪያ ካልያስያዙ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።

8. ተጫራቾች ሎት 1 ፣ ሎት3 ፣ ሎት4 ፣ ሎት7 እና ሎት9 ላይ ተጫራቹ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለበት። በተጨማሪም ሎት5 (የተለያዩ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች) ተጫራች የሚወዳደርበትን እቃ በከለርየተደገፈ ፎቶ እንደሳምፕል ማቅረብ ይኖርበታል።

9. ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ(specification) ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም።

10.በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ የራሳቸው እሴት የሌላቸው እና አምራች ያልሆኑ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ(C.P.O) 2% ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ። ሲፒዮ በጥቅል ማሰራት አይፈቀድም።

11.የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በመንግሥት የሥራ ሰዓት የት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማቅረብ እና የማስረከብ ግዴታ አለበት ከሥራ ሰዓት ውጪ የሚያመጣ ነጋዴ ተቀባይነት አይኖረውም ።

12.ለጨረታ ከቀረቡ እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሀያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13.ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦ ስ.ቁጥር 011-2-73-10-15

አድራሻ፡- አስኮ ሊዝ መንደር ከሚረር አካዳሚ ት/ቤት ጎን አቢሲኒያ ባንክ ፊት ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ት መምሪ የፊትአውራሪ

ኃ/ጊ/ቁ2 1ኟ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender