Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ ሎት2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ሎት3 የህትመት ውጤቶች ሎት4 የመኪና ጎማ የመኪና መለዋወጫዎች ሎት5 የፈርኒቸር ስራ ሎት6 የፅዳት እቃዎች ሎት7 የውኃ እቃዎች በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ ሎት2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ሎት3 የህትመት ውጤቶች ሎት4 የመኪና ጎማ የመኪና መለዋወጫዎች ሎት5 የፈርኒቸር ስራ ሎት6 የፅዳት እቃዎች ሎት7 የውኃ እቃዎች በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟስ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን

1. ከሚወዳደሩት ስራ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer Identificatin Number) ያላቸው፣

3. በግዥ አፈጻጸም መመሪያው የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ውጪ የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

5. የሚገዙ የእቃችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናውን የገቢ ደረሰኝ/ ማስያዝ አለባቸው፣

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን 100(አንድ መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4፡ 00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

10. ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

11. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የፃ/ወ/ገ/ፅ/ቤት

Save Tender