Tender Detail

Tender Details

በ2018 በጀት ዓመት በሁላ ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አማካይነት ለተለያዩ መ/ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የአዳራሽ መጋረጃዎች፣ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም ለሀ/ሰላም ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሀ/ሰላም ከተማ በሰቻና በሽቆ ቀበሌያት የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መንገድና አንድ የመኪና መንገድ ድልድይ ስራ እና ለወረዳው ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ አጥር በቆርቆሮ ለማሳጠር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

የጨረታ ማስታወቂያ

በዚሁ መሰረት፡-

  • በግንባታ ዘርፍ ደረጃ -9 ንግድ ፈቃድ እንዲሁም በሌሎች በየዘርፉ የዘመኑን ግብር የገበሩና ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣
  • መልካም የስራ ምስክርነት ወይም አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  • የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond/ Security) አጠቃላይ ለውድድር ካስገቡት መወዳደሪያ ዋጋ ላይ 2% ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከ01/13/2017 ዓ.ም እስከ 16/1/2018 ዓ.ም የማወዳደሪያ ሰነዱን ከሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በማሳየት መውሰድ ይችላሉ፡፡ አንድ ተጫራች ከአንድ ሰነድ (ሎት) በላይ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን በኦሪጅናልና በኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ በሁለቱም ፖስታ ላይ የድርጅቱን አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና በሰነዱ ላይ ፊርማ በማኖር ታሽጎ በሌላ ትልቅ ባለ ፖስታ ውስጥ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ፖስታዎች በማስገባት ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡ በ22ኛው ማለትም በ19/01/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት በሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡40 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 22ኛው የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ጨረታው ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፡፡

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender