Tender Detail

Tender Details


የድሬዳዋ አፈተኢሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም አላቂ የቢሮ እቃ፤ የትምህርት እቃ፤ የፅዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤ የላብራቶሪ እቃ፤ የህንጻ እቃዎች ግዢ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፈተኢሳ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የድሬዳዋ አፈተኢሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም አላቂ የቢሮ እቃ፤ የትምህርት እቃ፤ የፅዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤ የላብራቶሪ እቃ፤ የህንጻ እቃዎች ግዢ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ

  1. ተጫራቾች አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  2. የምዝገባ ፈቃድ ያላቸው
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  4. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ መክፈል ይኖርባቸዋል
  5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን መጥታችሁ ከቢሮ ቁጥር 24 መግዛት ትእላላችሁ።
  6. ጨረታው በተዘጋበት እለት /በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ት/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል የሚነበብ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00 (ሶስት ሺ) ጥሬ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር በት/ቤቱ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ገብቶ ስራውን መስራት ይኖርበታል።

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፈተኢሳ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender