የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም የቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ በዘርፉ ከተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም የቢሮ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም የቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያ በዘርፉ ከተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ -
1. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
2. በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
3. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የጽሕፈት መሳሪያ ለ3 ወራት በሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፤ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን በዓልም፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጽሕፈት መሳሪያ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ሶስት ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳየት አለበት፡፡
9. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ድጋፍ የሥራ ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር የማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-87-47 መደወል ይችላሉ።
