Tender Detail

Tender Details


በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/10 ፋይናንስ/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የኛ ዙር ጨረታ የተለያዩ እቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/10 ፋይናንስ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/10 ፋይናንስ/ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የኛ ዙር ጨረታ የተለያዩ እቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት

ሎት1፤ የሰራተኞች ደንብ ልብስ

ሎት2፤ የቢሮ አላቂ እቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች

ሎት3፡ የጽዳት እቃዎች

ሎት4፤ ኤሌክትሮኒክ እቃዎች ጥገና

ሎት5፤ ቋሚ እቃዎች ግዥ

ሎት 6፤ ህትመት ውጤቶች

ሎት7፤ ትራንስፖርት (የመኪና ኪራይ)

ሎት8፤ መስተንግዶ አቅርቦት

ሎት9፤ የዲኮር ኪራይ፤ የጀኔሬተር ኪራይ ፡የሞንታርቦ ኪራይ እና የድንኳን ኪራይ

ሎትıዐ፤የጉልበት ስራዎች፤ ኤሌከትሪክ ስራዎች፤ የፈርኒቸር እቃዎች ገጠማ ስራ እና ጥገና ስራዎች ;

ሎት11፤ የስልክ ገመድ /መስመር ዝርጋታ ስራዎች

ሎት12፤ የመኪና እቃ ግዥ

ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች/አገልግሎት/ ለማቅረብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾችን ከሎት1-6 ለተጠቀሱት እቃ/ተያያዥ አገልግሎቶች/ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ vat ተመዝጋቢ የሆኑ፤ አቅራቢነትና TIN no ከጨረታ ሰነዱ ጋራ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ነገር ግን ሎት 7 እስከ 12 የሚያቀርቡ ድርጅቶች/ግለሰቦች/ከላይ ከተጠቀሱ መስፈርቶች በተጨማሪ ቫት ወይም ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ኮ/ቀ/ወ/ 10 ፋ/ፅ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው በመውሰድ የዕቃዎች ዝርዝር ዋጋ ቫትን ጨምረው በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ/ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸው። የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፤30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች መስሪያ ቤቱ በሸጠላቸው መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው መመለስ የሚኖርባቸው ሲሆን የዕቃውን ዝርዝር ሞልቶ ለመላክ ቦታ ያንሳል ካሉ በተጨማሪ በራሳቸው ወረቀት በመሙላት የኃላፊ ፊርማና ህጋዊ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ወረዳው ከሸጠላቸው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች በሚያቀርቡትየመወዳደሪያ ዋጋ ሰነድ ላይ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የጨረታ ሰነዱ ሙሉ ክፍል አብሮ የሚመለስ ይሆናል። ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ የዕቃው ዓይነት /ብራንድ/ዕቃው የተመረተበት አገር በግልጽ የተጠቀሰ መሆን አለበት። እንዲሁም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት እቃዎች ናሙና ኦርጂናል/ትከከለኛነት/ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ በሚቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የተከፋፈለ ሲሆን ሎት1፤ 10,000(አስር ሺህ ብር) ሎት 2፤ 10,000(አስር ሺህ ብር) ሎት3፡ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት 4፤5000/ አምስት ሺህ ብር/ ሎት 5፤ 5000(አምስት ሺህ ብር) ፡ ሎት6፣5000(አምስት ሺህ ብር)፡ ሎት7፤2000(ሁለት ሺህ ብር) ሎት8፤ 5000(አምስት ሺህ ብር) ሎት9፤3000(ሶስት ሺህ ብር) ፤ሎት10፤1500(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ሎትከ፡ 4000አራት ሺህ ብር፤ሎት12፡2000(ሁለት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

መስሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾች ከመረጠ በኋላ ከሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም። በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለጻላቸው በኋላ በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ለግዢ ፈፃሚው አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውል መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው። ተጫራቾች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም። በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ፣መጫኛ እና ማውረጃ ወጪ ጨምሮ በወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ የሚያቀርቡ ይሆናል። መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በጥቃቅን የተደራጁ አካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ በጽ/ቤቱ ስም፣የጨረታ ቁጥሩን እና ከላይከሎት 1-8 በተገለፀው መሰረት የእቃን ወይም የአገልግሎቱን አይነት የሚገልጽ ባደራጃቸዉ ጽ/ቤት ሃላፊ ፊርማ የተፈረመ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪ በጥቃቅን የተደራጁ ድርጅቶች አምራች የሆኑ ብቻ ይሆናሉ፤ በተባለው መሰረት ያላቀረቡ ድርጅቶች የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፤ሁሉም የሚቀርቡ ሰነዶች ሌሎቹም በአማርኛ የተፃፉ መሆን አለባቸው ። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112739258/ በኮ/ቀ/ከ/ከ/ወረዳ 10ፋ/ጽ/ቤት18 ማዞሪያ በተለምዶ መላጣ ሜዳ የሚባለው ከመብራት ሀይል ከፍ ብሎ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 ላይ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender