Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሥሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 533 6497
  • Website
  • Deadline18 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Carpets And Curtains , Printing And Publishing , Cloth And Shoes

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለኤጀንሲው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች ሎት፡1 አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 2፡-ደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች እና ሎት 4 የኢቨንት ስራዎች፣ ሎት 5 የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሥሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለኤጀንሲው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች ሎት፡1 አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 2፡-ደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች እና ሎት 4 የኢቨንት ስራዎች፣ ሎት 5 የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደርኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።

2. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር /በመከፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ ዋስትና የንግድ ማዕከል 5ኛ ፎቅ ከግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ህጋዊ ሥልጣን ያለውን አካል ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው የሥራ ቀን 1፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋስትና የንግድ ማዕከል 5ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ነገርግን 11 ኛው ቀን በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይየሚከፈት ይሆናል።

5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% Unconditional Bank Guaranty ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው። እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴከኒከና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0115336497

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ

Save Tender