በደ/ኢት/ክ/መ/ የደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የሌሞ-ጌንቶ ጤና ጣቢያ የቀዶ ጥገና ክፍልን ለማስጠገን በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን የጉልበት ዋጋ ከነሙሉ ግንባታ ግብዓት እና ቁሳቁስ (ተርንክይ) በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በደ/ኢ/ክ/መ/ በደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢት/ክ/መ/ የደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የሌሞ-ጌንቶ ጤና ጣቢያ የቀዶ ጥገና ክፍልን ለማስጠገን በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን የጉልበት ዋጋ ከነሙሉ ግንባታ ግብዓት እና ቁሳቁስ (ተርንክይ) በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት፡-
- በግንባታ ዘርፍ የደረጃ GC-9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የግንባታ ማህበር፤
- በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በክልል ኮንስትራክሽን ቢሮ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግበው የ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋጋጫ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ለ2017 የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የግብር ግዴታቸውን በመወጣት ሥልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለሥልጣን ለበጀት ዓመቱ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ሠርተፊኬት የያዙ /valid tax Clearance certificate for 2016 E.C budget year/
- በፈዴራል ወይም በክልል የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን የሚመለከው አካል በዘርፉ በተቋራጭነት በተቋራጮች ዝርዝር የተመዘገበ /Registered in FPPA or PPA Contractors List/
- ከዚህ ቀድም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራዎችን በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረከብ ስለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል፣ ማዘግየት፣ ውል ማቋረት ወይም የውል አስተዳደርና አፈፃፀም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ሥልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ማንኛውም የመንግስት አካል ማስረጃ ያለው በመሆኑ ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀክቱ የውል እስፔስፊኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈልገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቂያ ለአሰሪ ባለበጀት መ/ቤቱ በወቅቱ ያላስረከቡ፣ ውል ያቋረጡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡ ስለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጪ ይደረጋሉ ወይም ይሰረዛሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ የጽሑፍ ማመልከቻ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከማሌ ወረዳ ፋይናንስ ግ/አስ/ክፍል የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- በተጨማሪ የጨረታ ዝርዝር መስፈርት ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ከታወቀ ባንክ ወይም ከፋይናንስ ተቋም በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ የጨረታው ቴክኒካል ኦሪጅናል ዶክሜንት ጋር በአንድ ፖስታ ማስያዝ አለባቸው።
- ለግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (ቁሳቁሶች) በሙሉ በአሸናፊ ተጫራች የሚቀርብ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሰነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያዩ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን የስራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሠዓት በኋላ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
የጨረታው አከፋፋት ስነ-ስርዓትም፡- በሁለቱም ቴክኒካሉ እና ፋይናንሻሉም በአንድነት ተከፍቶ የሚገመገም ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 09-80-39-88-24/ 09-12-84-57-64 በመደውል መረዳት ይቻላል።
በደ/ኢ/ክ/መ/ በደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
