Tender Detail

Tender Details

  • Company ደቡብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-51-31
  • Website
  • Deadline12 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-09-15 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

ደቡብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር የኩባንያውን የ2016 እና 2017 በጀት ዓመት ሂሳብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ደቡብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ


 

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ደቡብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር የኩባንያውን የ2016 እና 2017 በጀት ዓመት ሂሳብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ስለሚፈልግ መስፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶችን ለዚህ ሥራ ውድድር ለመጋበዝ ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማቅረብ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

ስለዚህ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መስፈርቶች፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN-No) ያላቸው።
  2. በዘርፉ ሕጋዊ የሙያ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  3. በአዲሱ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃ በ(IFRS) ከሕጋዊ ተቋም ሰርተፊኬት ያለው፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ቢጋር (TOR) የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ተረከበው የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ለመወዳደር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩበትን የተሟላ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሠነድ “ኦሪጅናል" እና “ኮፒ” በሚል ተለይቶ ከእያንዳንዱ 2 ኮፒ በሰም በታሸገ በተለያየ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ይህ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በ7ኛው የሥራ ቀን በ11፡30 ታሽጎ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ቴክኒካል ፕሮፖዛሉ በ8ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛሉ በ10ኛው ቀን በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. ነገር ግን የቴክኒካል ፕሮፖዛሉ የማጣራት ሥራው ከ10ኛው ቀን በፊት ወይም በኋላ የሚጠናቀቅ ከሆነ ለተወዳዳሪዎች በስልክ ወይም በቴሌግራም ይገለጽላቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  12. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ደቡብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-212-51-31 (ሀዋሳ)

 

ደቡብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ

 

Save Tender