Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶሳ ወዩ ከተማ ገ/ጽ/ቤት
  • Address በጉጂ ዞን የአዶሳ ወዩ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0926459874
  • Website
  • Deadline23 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityከጠቅላላው የግዥ ዋጋ 2%
  • opening date2025-09-24 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Electronics Materials

በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶላ ወዩ ከተማ ዝጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ (furniture) /2018 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶሳ ወዩ ከተማ ገ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶላ ወዩ ከተማ ዝጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ (furniture) /2018 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ቀርባቹ መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች በዚህ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ስለመሆናቸው ህጋዊ የታደስ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡና ስለ ቀድሞ መልካም አፈጻጸም መረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በመደበኛ የስራ ሰዓት በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በአዶላ ገ/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የግዥ ዋጋ 2% በአዶላ ወዩ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ከዋናው (Orjinal) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ ለተሸናፊ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን ጨረታውን ላሸንፋት የሚመለሰው ደግሞ የውል ማስከበሪያ በአዶላ ገ/ጽ/ቤት ካስገቡ በኋላ ነው፡፡
  5. የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች በሰም በታሸገ ፖስታ (envelope) ዋናውንና ኮፒውን ለያይቶ ይህ ማስታወቂያ ከታተመበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ እና በ15ተኛው ቀን ከቀኑ እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ በአዶላ ወዩ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ጨረታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ተጠናቆ በማግስቱ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው /ተዛቢዎች በተገኙበት በአዶላ ገ/ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መክፈት እያስተጓግለውም ፡፡
  7. የኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎች ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረቢያቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በማለያየት በሰም በታሸገ ፓስታ (envelope) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናቶች ውስጥ እና በ15ተኛው ቀን ከቀኑ እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ በአዶላ ወዩ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ 15 የሰራ ቀናቶች ከተጠናቀቀ በኋላ በሁለተኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዶላ ገ/ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ የጨረታው ሰነድ ይከፈታል፡፡ ቢሆንም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መክፈት እያስተጓግለውም፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን እቃ በሙሉ በአዶላ ገ/ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ያስረክባል፡፡
  10. ጨረታው የሚካሄደው አፋን በኦሮሞ ቋንቋ ይሆናል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡-  በስልክ ቁጥር 0926459874 ወይም 0911095662 ይደውሉ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶሳ ወዩ ከተማ ገ/ጽ/ቤት

 

Save Tender