Tender Detail

Tender Details


የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክል፤ ጎማዎች፤ ባትሪዎች እና አሮጌ የተሽከርካሪ አካሎች ባሉበት ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት


የጨረታ ማስታወቂያ

የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክል፤ ጎማዎች፤ ባትሪዎች እና አሮጌ የተሽከርካሪ አካሎች ባሉበት ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተሸከርካሪዎቹ እና ንብረቶቹ ካሳንቺስ ኢሲኤ (ECA) ጀርባ ባለው መ/ቤታችን ይገኛሉ፡፡

1. ማንኛውም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ3፡00 - 10፡00 ሰዓት ማየት ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች የንብረቱ መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ አዲስ አበባ በሚገኙ ቅርንጫፍ ባንኮች ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ጨረታው መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

4. አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለአገልግሎት መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር ፡-011 126 14 70 ወይም 011 123 84 64

ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት

Save Tender