አመን የበጎ አድራጎት ማህበር የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶችን በውጭ ኦዲተር ኦዲት ለማስደረግ በግልጽ ጨረታ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
አመን የበጎ አድራጎት ማህበር
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አመን የበጎ አድራጎት ማህበር የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነዶችን በውጭ ኦዲተር ኦዲት ለማስደረግ በግልጽ ጨረታ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ ያለችሁ አዲተሮች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
- የምዝገባ ሰርተፊኬት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆነ የምዝገባ ሰርተፊኬት
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ላይ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመጻፍ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ሲገለጽ የሚፈለገውን አገልግሎት ወዲያውኑ ያቀርባል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቂ/ክ/ከተማ በሚገኘው ጨርቆስ የገበያ ማዕከል ቁጥር 62 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡-
በ0911223526/0911973730 ይደውሉ።
አመን የበጎ አድራጎት ማህበር
