Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-637-50-23
  • Website
  • Deadline16 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለጽህፈት መሳሪያ 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-16 00:00:00
  • Categories Veterinary Equipment And Supplies , Stationery Materials , Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2፡- የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሎት 3፡- የእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍና በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2፡- የመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሎት 3፡- የእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍና በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መሞላት የሚገባውን መረጃ ሁሉ በትክክል በመሙላት እና በመፈረም አንድ ኦርጅናል ፖስታ የራሳቸውን ፊርማና አድራሻ ተፅፎበት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ከቢሮ ቁጥር 20 በመግዛት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።
  4. ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም። ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በቁርጥ ለጽህፈት መሳሪያ 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለመኪና ጎማ ከነከመናዳሪውና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለእንሰሳት መድሃኒትና መገልገያ መሳሪያዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማሲያዝ አለባቸው።
  6. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
  7. በሎት 3 ላይ የተጠቀሰው የእንስሳት መድሀኒት እና መገልገያ መሳሪያዎች ግዥን በተመለከተ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ጅምላ አከፋፋዮች ብቻ በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ 10% የውል ማስከበሪያ በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ እና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-637-50-23 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

 

የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender