Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቡቃያ ቅድመ ፀኛ እና የኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 የግዥ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቡቃያ ቅድመ ፀኛ እና የኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት/ የደንብ ልብስ፣ ሎት2/ አላቂ የጽሕፈት ዕቃዎች፣ ሎት3/ የሕከምና ዕቃዎች፣ ሎት4/ የሕትመት ሥራዎች፣ ሎት5/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት6/ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት7/ ቋሚ ዕቃዎች ሎት8/ የተለያዩ የሕንፃ መሣሪያዎች (ዕቃዎች)፣

ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ ቲን/ቁ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ. ቁ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዶችን ሲያስገቡ የተገለጸውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

6. ለተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎትı/ የደንብ ልብስ 4,000.00 (አራት ሺህ ብር)፣ ሎት2/ አላቂ የጽሕፈት ዕቃዎች 4,000.00 (አራት ሺህ ብር)፣ ሎት3/ የሕከምና ዕቃዎች 4,000.00 (አራት ሺህ ብር)፣ ሎት4/ የሕትመት ሥራዎች 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) ሎት5/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 4,000.00(አራት ሺህ ብር) ፤ ሎት6/ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) | ሎት7/ ቋሚ ዕቃዎች 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) ሎት8/ የተለያዩ የሕንፃ መሣሪያዎች (ዕቃዎች)4.000.00 (አራት ሺህ ብር)፣ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይ/ግዢ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦሪጅናል እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ተቋሙ የሸጠውን ሰነድ መመለስ አለባቸው ከዛ ውጪ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

 

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ነገር ግን ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን የማይገልጽ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

10. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

11.የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 በት/ቤቱ ፋይ/ግዢ ከፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡

12. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

13. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ከኬንያ ኢምባሲ 500 ሜትር ወደላይ በሚወስደው አስፋልት ገባ ብሎ ዳዊት ጋራዥ አጠገብ ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁ 0116663282/0116662717

የቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender