የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
-
ሸቀጣ ሸቀጥ የምግብ
-
የፅዳት እቃዎች
-
የፅህፈት መሣሪያ
-
የጤፍ ዱቄት
-
የአሣና የአሣ ውጤቶች
-
ወተት
-
ሽሮና በርበሬ
-
አትክልትና ፍራፍሬ
-
የወተት ተዋፅኦ(የቺዝ)
-
ስጋና የስጋ ውጤቶች
-
እንቁላል፣ ቅቤ እና አይብ
-
የሰራተኞች አልባሳት
ስለሆነም ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
-
ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉና በዘርፋ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ሰርተፍኬት)፣ የገቢዎች የግብር ከፋይ ከሊራንስ ሰርተፍኬት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ከለብ ግዥ ከፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር በመከፈል ሠነድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 ለእያንዳንዱ ሰነድ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒአ) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስት ሆኖ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ሕጋዊ ማህተም በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ለዚህ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
-
ዘግይተው የሚደርሰ ማንኛውንም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
-
ጨረታ አሸናፊዎች ማሸናፋቸውን በጽሑፍ የሚገለፅላቸውንና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል፡፡
-
ሕጋዊ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ በእለቱ ከጨረታ ተወዳዳሪነት ውጪ ይሆናሉ፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር- 011369-15-33 /0940248638 በመደወል ወይም አድራሻ ጦር ኃይሎች ሞቢል ፊት ለፊት ኡማ ሆቴል 100 ሜትር ገባ ብሎ በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ
