በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የቤተሰብ ምዝገባ ቅጽ 001፤ ያላገባ ሰርተፍኬትና የነዋርነት መታወቂያ ካርድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት የቤተሰብ ምዝገባ ቅጽ 001፤ ያላገባ ሰርተፍኬትና የነዋርነት መታወቂያ ካርድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚህም መሠረት፤-
-
ህጋዊ ንግድ ፍቃድና TIN NO ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
-
የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ነው፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠ6ኛው ቀን ከቀኑ 8፤30 ሰዓት ይታሸግና ወዲያውኑ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
VAT ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
-
ተጫራቾች ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሠነዶችን ለይተው በሁለት ፖስታ በሰም ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡ ፡ በተጨማሪም አሸናፊ ው ተጫራች የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ አነስተኛ ዋጋ ላሳዩ ግዥዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
-
የቀረቡ ማወዳደሪያ ሃሳቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ጸንቶ የሚቆዩ ማስተካከያ የማይደረግላቸውን መሆናቸውን እናረጋግጣለን፡፡
-
የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ሽያጭ 2% ከባንክ የተረጋገጠ /CPO/ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የጨረታ ሠነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 /በፊደል ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 የከፈሉበትን ደረሰኝ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፤ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /ሞባይል/ ቁጥር 0916020865/0916516908 አድራሻ፤ ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
