የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚከተሉትን እቃዎችና አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚከተሉትን እቃዎችና አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት1 የፈርኒቸር ግዥ 30,000.00
ሎት2 የመኪና ወንበር እድሳት 10,000.00
ሎት 3 የአልሙኒየም እቃዎች ግዥ 20,000.00
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ።
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ባለው ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከሎት1-ሎት 3 ላሉት እቃዎች ላቀረቡት ጠቅላላ የጨረታ ማስከበሪያ ሎቶች ፊት ባለው ዋጋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የታሽገ እና በማህተም የተመታ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለአንድ እቃ አንድ ዋጋ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል ማጫረት ይችላሉ፣
- የጨረታ ሰነዱን ማቅረቢያ የመጨረሻው ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ሆኖ በ11ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል 4፡00 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ይሆናል፡፡ ሆኖም አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም ጽ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃዎች ናሙና በሙሉ በየሎቱ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው፤
- ተጫራቾች የወሰዱትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መቀየር አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራቻቸው ተቋም ሰነድ የሚወስዱበትና የውል ዋስትና ደብዳቤ ማፃፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫት ማካተት አለባቸው።
አድራሻ፡- ቤቴል አደባባይ ዝቅ ብሎ ፖስታ ቤት ፊለ ፊት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0113696984/0113697912
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት
